ጥቃቱ የተፈጸመው ወደ መተከል ዞን ዋና ከተማ ግልገል በለስ
ጥቃቱ የተፈጸመው ወደ መተከል ዞን ዋና ከተማ ግልገል በለስ ጥቃቱ የተፈጸመው ወደ መተከል ዞን ዋና ከተማ ግልገል በለስ
By Brook News Admin
2d ago · 1 min read
ጥቃቱ የተፈጸመው ወደ መተከል ዞን ዋና ከተማ ግልገል በለስ እየተጓዙ በነበሩ አራት ተሽከርካሪዎች ላይ በዳንጉር እና ጉባ ወረዳዎች መካከል ላይ አይሲድ ቀበሌ ወይም አፍሪካ እርሻ ልማት በተባለ ስፍራ ላይ መሆኑን ቢቢሲ ተረድቷል።
ፀሐይነሽ ህመም ላይ ያሉ እናቷን ለመጠየቅ ሕጻን ልጇን ይዛ ወደ ቡለን ወረዳ እየተጓዘች በነበረችበት ጊዜ ነው ታጣቂዎቹ በፈጸሙት ጥቃት ከነ ልጇ የተገደለችው።
"ከዚህ ቀደም አባቷን ሳታይ ስለሞቱባት፤ እናቷን 'ሳላያት እንዳትሞት' በማለት ከ13 ዓመታት በኋላ እናቷን ልታይ እየሄደች ነበር" ሲሉ አንድ የቤተሰብ አባል እናት ከልጇ ጋር እንደወጣች የቀረችበትን አጋጣሚ አስረድተዋል።
የቤተሰብ አጋዥ እና ወንድሞቿን የምታስተምር እንደሆነች የተናገሩት ቤተሰቡ፤ "ያላለቀሰ ሕዝብ የለም" በማለት የእናት እና ልጅ ግድያ በማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ሐዘን እና ድንጋጤን መፍጠሩን ገልጸዋል።
ሚስቱ እና ልጁ በታጣቂዎች የተገደሉበት በባለቤቷ በከፍተኛ ሐዘን ምክንያት በመረበሹ ራሱን እና ሌሎችን እንዳይጎዳ በሚል "ታስሮ" እንደሚገኝ የቤተሰብ አባሉ ተናግረዋል። BBC Amharic
Filed under