በአሜሪካ AI አስደንጋጭ ነገር ፈጠረ❗️ 🇺🇸 አንትሮፒክ የተባለው ታዋቂ የAI ኩባንያ የክላውድ ቻት ቦት ሰሪ ሲሆን በውስጥ የሙከራ ስራ ላይ የነበረ ሲክተም ከቁጥጥር ውጪ ወተው እጅግ አሳሳቢ ነገር አድርገዋል። በዚህ ባልተጠበቀ እና አደገኛ ድርጊት በነጩ ቤተመንግስት ስብሰባ ተቀምጠዋል። 🇺🇸 የሐሰት የግድያ ጥቆማ ፣ የኩባንያው AI ሞዴል በፍላዴልፊያ ፖሊስ ድረ-ገጽ ላይ ግድያዎችን ለመጠቆም በተዘጋጀ ፕላትፎርም እንደ እውነተኛ ሰው በመቅረብ የሐሰት ግድያ ጥቆማ ልኳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዳግመኛ ተመርጠዋል❗️ 👉የገንዘብ ሚኒስትርን ጨምሮ አራት የካቢኔ አባላት እስካሁን ከሀላፊነት መነሳታቸው ታውቋል፡፡ ይህም በአዲሱ ካቢኔ እንደማይካተቱ ያሳያል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ፣ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫቱ ሳኒ ፣ የመስኖና እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) እና የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፡፡ እስካሁን ከሚኒስትርነት ሀላፊነታቸው ተነስተው በሌሎች የስራ ሀላፊነቶች ላይ የተሾሙ ናቸው፡፡ የገንዘብ ሚኒስትር የነበሩት አቶ አህመድ ሺዴ ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው የመንግስት መስረታ የተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ተደርገው ተሹመዋል፡፡ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልም ፌደሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ተደርገው ተሰይመ

ኢትዮጵያ በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን እንዲዘጋ መወሰኗን አስታወቀች። በአዲስ አበባ የሚገኙ 10 ኤርትራውያን ዲፕሎማቶችም በ48 ሰዓት ኢትዮጵያን ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥታለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ሐሙስ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፤

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሹመቶችን አጸደቀ መስከረም 20፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ያቀረቧቸውን አራት ሹመቶች አጽድቋል። በዚህም የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማዋ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል። እንዲሁም አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ፤

🛰ራሺያን ለመምታት ኤለን መስክ ድጋፍ ተጠየቀ❗️ 👉ዘ ጋርዲያን እና ሮይተርስ እንደዘገቡት፣ የፊንላንዱ ፕሬዝዳንት ስተብ በኒውዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከኢሎን ማስክ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የስታርሊንክ (Starlink) ሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎት በሩሲያ ግዛት ውስጥም እንዲሠራ እና ዩክሬን እንድትጠቀምበት ጠይቀዋል። 👉🛰 በእጅጉ እየወደመች ያለችው ዩክሬን የአየር መከላከያ ሚሳይሎች እጥረት ስለገጠማት፣ ሩሲያ በግዛቷ ውስጥ ሆና ወደ ዩክሬን የሚሳይል ጥቃት የምታደርስባቸውን ተንቀሳቃሽ የባሊስቲክ ሚሳይል ማስወንጨፊያዎች፤ የስታርሊንክን ሳተላይት እና ድሮኖችን በመጠቀም አድራሻቸውነሰ አውቃ ቀድማ ለመምታት አቅዳለች።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠናቀቅን ተከትሎ አዲሱ የፌዴራል መንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በመጪው መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚከናወን አስታወቁ። አፈ-ጉባኤው ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተሳተፉበት ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸው፣ በሕገ-መንግሥቱ መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘው አካል ቀጣዩን የ5 ዓመት የሀገር መሪነት ኃላፊነት እንደሚረከብ አረጋግጠዋል።

በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ባቀረቡ ቅሬታ መሰረት በሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጊዚያዊነት እንዲመደቡ ተወሰነ። ትግራይ ክልል ባለው ነባራዊ ሁኔታ በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በክልሉ አስቻይ ሁኔታ እስኪፈጠር በሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጊዚያዊነት እንዲመደቡ መወሰኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ። ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩና በአሁኑ ወቅት በክልሉ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ትምህርታቸውን መቀጠል ባለመቻላቸው ለቅሬታቸው መፍትሔ ለመጠየቅ በትምህርት ሚኒስቴር ግቢ ከተገኙ ተማሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ከፍተኛ ገንዘብ ተሸለመች💰 አትሌት ልቅና አምባው የ5000 ሜትር የአልቲሜት ሻምፒዮና አሸናፊ ሆነች 💎በአልቲሜት ሻምፒዮና የመጨረሻ ቀን በተካሄደው የሴቶች 5000 ሜትር ፍፃሜ ውድድር አትሌት ልቅና አምባው በአስደናቂ አቋም ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቅ የሻምፒዮናው አሸናፊ ሆናለች። 💎አትሌት ልቅና 5000 ሜትሩን 14:30.36 በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፍ ችላለች። 💎በውድድሩ የኢትዮጵያ አትሌቶች ጥሩ ውጤቶችን ያስመዘገቡ ሲሆን፣ አትሌት ፋንታዬ በላይነህ 14:32.62 በሆነ ጊዜ ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ አሸንፋለች።

🇺🇸ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መግባት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን የፍልሰት ጉዳዮች ለማስተናገድ፤ የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት በኢትዮጵያ የሚከፍተው ቢሮ በነገው ዕለት ስራ ይጀምራል። 👉በቢሮው ለመስተናገድ የሚሹ ኢትዮጵያውያን አስቀድመው ቀጠሮ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው አገልግሎቱ ገልጿል።
🎧 ፖለቲከኛው ሙዚቀኛ ሊሆኑ❗️ልደቱ አያሌው የሙዚቃ አልበም ሊለቁ ነው! ላለፉት ሶስት አስርት አመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚታወቁት አቶ ልደቱ፤ ሀሳብን በዜማ በሚል ለአዲስ አመት የሙዚቃ አልበም ሊያሰራጩ መሆኑን ገልጸዋል።

ማለዳውን 1:50 ሠዓት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ11 ልዩ ቦታው ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤ/ክርስቲያን አካባቢ ነው፡፡ የጉዞ አቅጣጫው ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ የሆነ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-05997 ትግ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በተጠቀሰው አካባቢ በመንገድ ስራ ላይ የነበረ ስካቫተር ማሽን መቆፈሪያው ወድቆበት በታክሲው ውስጥ ከነበሩ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች መካከል የ5 ወንዶችና 1 ሴት ህይወት አልፏል፡፡ ከሟቾች በተጨማሪ በታክሲ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ የሚገኙ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡ via_AddisAbabaPolice ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያቀረበው አቤቱታ እና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ! በምክክሩ ወቅት አዳዲስ ተሳታፊዎች ግልጽነት በጎደለው መንገድ እየተጨመሩ መሆኑን፣ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ከተመደቡበት ቡድን ውጭ በመግባት ተፅዕኖ እያሳደሩ እንደሚገኙ እና ሂደቱ ቀድሞ ወደተወሰነ የፖለቲካ አቅጣጫ እየተመራ ነው ሲል አብን ይከሳል። የባለሙያዎች ፓነል ገለልተኝነት የጎደለው መሆኑን እና የአንድን ወገን የፖለቲካ ትርክት ለማስረጽ እንደሚሞክርም የ አብን ደብዳቤ ይገልጻል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ የጾመ ማርያም (የጾመ ፍልሰታ) ወቅት ባስተላለፉት መልእክት የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አጉልተው አሳስበዋል ምዕመናን የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ የታመሙትንና የታሰሩትን በመጠየቅ፣ እንዲሁም ንስሐ በመግባትና ቅዱስ ቁርባን በመቀበል እንዲያሳልፉ አባታዊ ጥሪ አቅርበዋል። አምላክን መውደድ በስሜት ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን ትእዛዛቱን በመጠበቅና በመተግበር የሚረጋገጥ ተግባራዊ ሕይወት እንደሆነ ገልጸዋል። ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ» ሲባል የተወሰነ የኅብረተሰብ ክፍልን ብቻ ሳይሆን በሕይወት ያሉትንም ሆነ ያለፉትን—መላውን የሰው ልጅ የሚያጠቃልል እንደሆነ አብራርተዋል።

በዓለም ላይ በዕድሜ አንጋፋው የሀገር መሪ የሆኑት የካሜሩን ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ ከህዝብ እይታ ከራቁ ሁለት ወራት ተቆጥረዋል። እሳቸው ለቀጣይ "አጭር የግል ቆይታ ወደ አውሮፓ" ጉዞ ማድረጋቸውን የሲቪል ካቢኔያቸው ቢገልፅም ሰኔ 7 ከካሜሩን ከወጡ በኋላ እስካሁን አልተመለሱም። ታዲያ አስገርስሚው ነገር እዛው ባሉበት አውሮፓ ሆነው ከፍተኛ የወታደራዊ አባላትን ሹመት አድርገዋል :: የፕሬዝዳንታዊ ዘብ ቡድን መሪን ከኮሎኔልነት ወደ ብሪጋዴር ጄኔራልነት እና ከአገሪቱ አምስት የጋራ ወታደራዊ ክልሎች የነበሩ የአራት ክልል አዛዦችን በመተካት ከፍተኛ የወታደራዊ አባላትን ሽግሽግ አድርገዋል።

በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 672 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ ስምንት ዙር በረራ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱት ዜጎች መካከል እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 34 ታዳጊዎች ይገኙበታል። መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ90 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል። በህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ህብረተሰቡን ለማስገንዘብ፣ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰትን ለማበረታታት የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አሳውቋል፡፡ መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ወደተለያዩ ሀገራት ሄደው የሚመለሱ የፍልሰት ተጎጂዎችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል እና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር፣ በብዙ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ላይ ከፍተኛ ኢሰብአዊ ድርጊት ሲፈጽም የነበረውን አድነው ባሻው ውዳሞ የተባለ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ በማላዊ አድኖ በቁጥጥር ሥር በማዋል ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ እንዳመጣው አሳወቀ። ተጠርጣሪው ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል (በተለይም ከሀድያ እና ከንባታ ዞኖች) ወጣቶችን "ሕይወታችሁን ታሻሽላላችሁ" በሚል አታልሎ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያዘዋውር የነበረ ሲሆን፣ ከእያንዳንዱ ተጓዥ ከ600 ሺህ እስከ 800 ሺህ ብር ይጠይቅ ነበር። ተጓዦችን በዕቃ መጫኛ ኮንቴነሮች፣ በተሳቢ እና በሸራ በተሸፈኑ መኪኖች አጭቆ ወደ ታንዛኒያ ካሻገረ በኋላ ጫካ ውስጥ ጥሏቸው ይፈረጥጥ ነበር።

የ20 ዶላር አታላይ ግለሰብ መታሰርን አስመልክቶ ይህንን ብሏል "ግለሰቡ እንዲታሰር ፍላጎት የለኝም። በችግር እና በተስፋ መቁረጥ ምክንያት የሚፈጠር ድርጊት መሆኑን ስለምረዳ፣ ገጠመኜን ያቀረብኩት ሰውን ለመቅጣት ሳይሆን የጉዞ ልምዴን ለማካፈል ነው።" "ላሊበላ በአውሮፓ ቢሆን ኖሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጎብኚዎችን ይስብ ነበር። ኢትዮጵያ ከዚህ ታላቅ የታሪክ ሀብቷ ተጠቃሚ እንድትሆን የተሻለ ድርጅታዊ አሰራር፣ ሙያዊ ስልጠና፣ ግልጽነት እና ኢንቨስትመንት ያስፈልጋታል።" ያለ ሲሆን ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ያለውን ዋና ዋና ነጥቦች አጋርቷል :: የ100 ዶላር የመግቢያ ክፍያ እና የአገልግሎት ክፍተት አለው ያለ ሲሆን ምክናየቱን እንዲ አጋርቷል "የ100 ዶላር ክፍያው ከመጠን ያለፈ ነው፤

በታሪካዊው የአዲስ አበባ ንግድ ባንክ (ክቡ) ሕንፃ ፊት ለፊት የሕንፃውን ውበት በእጅጉ የሚጎዳ የዘበኛ ቤት ቅጥያ ግንባታ ተካሂዶ ነበር። በማህበራዊ ሚዲያ፣ በሙያተኞች እና በብዙኃን መገናኛ በተደረገው ተፅዕኖ የሕዝቡ ድምፅ ተሰምቶ ግንባታው ሙሉ በሙሉ እንዲፈርስ ተደርጓል። ጉዳዩ ትኩት እንዲያገኛል ሲጥር የቆየው ኢ/ር ጌታሁን ሄራሞ አፋጣኝ ምላሽ ለሰጡት ምስጋናው አቅርቧል :: የአዲስ አበባ ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን፡ በኢ/ር ሕይወት ሳሙኤል የሚመራው ይህ ባለስልጣን ቅሬታውን ተቀብሎ ግንባታው እንዲፈርስ ግንባር ቀደም ሚና በመጫወቱ ተመስግኗል።

በዓለም ዋንጫው የአትሌቲኮ ማድሪድ የበላይነት! ለሶስተኛ ተከታታይ የዓለም ዋንጫ አትሌቲኮ ማድሪድ በግማሽ ፍጻሜው/በፍጻሜው ውድድር ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተጫዋቾች ያሉት ክለብ ሆኗል። 2018፡ 4 ተጫዋቾች በፍጻሜው ላይ 2022፡ 4 ተጫዋቾች በፍጻሜው ላይ 2026፡ 10 ተጫዋቾች በፍጻሜው ላይ በአጠቃላይ ከነበሩት 52 ተጫዋቾች መካከል 10 የአትሌቲኮ ማድሪድ ተጫዋቾች በፍጻሜው ጨዋታ ላይ በመሳተፋቸው ክለቡ የምንግዜውንም ከፍተኛ የ ተጫዋች ተሳትፎ ክብረወሰን ይዟል:: ለስፔን ብሔራዊ ቡድን (4 ተጫዋቾች) ማርኮስ ሎሬንቴ (Marcos Llorente) — ተከላካይ/አማካይ አሌክስ ባኤና (Álex Baena) — አማካይ ማርክ ፑቢል (Marc Pubill) — ተከላካይ አሌሃንድሮ ግሪማልዶ (Alejandro Grimaldo) — ተከላካይ 🇦🇷

የአሜሪካ ጦር በኢራን ላይ ለአምስተኛ ተከታታይ ቀናት አርብ ሐምሌ 11 ቀን ጥቃት ፈጽሟል። የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (US Central Command) ባወጣው የቪዲዮ ምስል እንደገለጸው ኃይሎቻቸው የክትትልና የስለላ ጣቢያዎችን የወታደራዊ ሎጅስቲክስ መሠረተ ልማቶችን እና የጦር መሣሪያ ማከማቻዎችን መትተዋል።

የአሜሪካ ጦር በኢራን ላይ ለአምስተኛ ተከታታይ ቀናት አርብ ሐምሌ 11 ቀን ጥቃት ፈጽሟል። የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (US Central Command) ባወጣው የቪዲዮ ምስል እንደገለጸው ኃይሎቻቸው የክትትልና የስለላ ጣቢያዎችን የወታደራዊ ሎጅስቲክስ መሠረተ ልማቶችን እና የጦር መሣሪያ ማከማቻዎችን መትተዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ዱባይ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በውጭ ሀገር ተደብቀው በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የነበሩ ዳውድ ተፈሪ ለገሰ እና ደስታ ተገኝ አበጋዝ የተባሉ አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ዱባይ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በውጭ ሀገር ተደብቀው በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የነበሩ ዳውድ ተፈሪ ለገሰ እና ደስታ ተገኝ አበጋዝ የተባሉ አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል። ሁለቱ ዋና ተጠርጣሪዎች የተለያዩ የማታለያ ዘዴዎችን በመጠቀም 105 ዜጎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ዱባይ በመውሰድና ከ188 ሚሊዮን ብር በላይ ከተጎጂዎች በመሰብ

በእግር ኳስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ (ፋይናል) ጨዋታ የእረፍት ሰዓት (Half-time)፣ የአሜሪካው 'ሱፐር ቦውል' አይነት ታላቅ የሙዚቃ ትዕይንት ለማስተናገድ ሲባል እስከ 25 ደቂቃ ሊረዝም እንደሚችል ታውቋል። ይህ ታሪካዊ ክስተት እሑድ በኒው ዮርክ ኒው ጀርሲ ስታዲየም በሚደረገው የ2026 ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ ይካሄዳል። ይህንን የሙዚቃ ትዕይንት የኮልድፕሌይ (Coldplay) ባንድ መሪ ክሪስ ማርቲን ያዘጋጀው (curate ያደረገው) ሲሆን፣ በዓለም ዙሪያ እጅግ ዝነኛ የሆኑ አርቲስቶች በአንድ መድረክ ላይ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

ከ2010 ዓ.ም ጀምረው እስከ 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ሳይፈተኑ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ የሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም የሶስተኛ ዲግሪ የያዙ ባሉበት የትምህርት (ለBA, MA, and PhD) ደረጃ ላይ ሚኒስትሩ በሚያወጣው በያዙት የትምህርት ደረጃ ፈተና ተፈትነው ሲያልፉ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው ይሆናል፡፡ በቀድሞው ዲፕሎማ ወይም ከ12+2 ወይም ከ10+3 ወይም ከቴክኒክና ሙያ ደረጃ አራት ስልጠና ተመርቀው ያጠናቀቁ ትክክለኛነቱ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወይም በፌደራል ወይም በክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም የተረጋገጠ ኦሪጅናል የስልጠና ማስረጃ ወይም ዲፕሎማ እና ትራንስክሪፕት ኖራቸው ነገር ግን የደረጃ አራት የብቃት ማዕቀፍ ሳይኖራቸው በመጀመሪያ ዲግሪ ተምረው የተመረቁ የትምህርት ማስረጃ የሚረጋገጥላቸው፦ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ይህ

ባለፉት 5 ዓመታት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበራቸው የሕዝብ ውክልና ትናንት በይፋ ማብቃቱን ተከትሎ የአገልግሎት ምዕራፍ ማጠቃለያ እና የቀጣይ ጉዞ ማስታወቂያ አጋርተዋል :: ጠቅላይ ሚኒስትሩ «አብረን እንስራ» በማለት ላቀረቡት ጥሪ እና በ7ኛው ዙር ምርጫ በባሕር ዳር ተወዳዳሪ ቢሆኑ ኖሮ እጩ ላለማቅረብ አስበው እንደነበርና በምክር ቤቱ ያነሷቸው ሐሳቦች ጠቃሚ እንደነበሩ ለገለጹላቸው አስተያየት እውቅና ሰጥተዋል። ላለፉት 10 ዓመታት ከነበረው ድካም በኋላ፣ አሁን ራሳቸውን ከማንኛውም ቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ (በአባልነትም ሆነ በደጋፊነት) ያገለሉ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይ በሙያቸው ሀገርን ማገልገል፣ በግሉ ሴክተር (Startups) ላይ መሰማራት እና ለቤተሰብ ጊዜ መስጠት ላይ ያተኩራሉ።

ከዚህ ቀደም በወጣው የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅ መሠረት፣ ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበረው ፍትሐዊ የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ መጽደቁን የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ። ይህንን ተከትሎ በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል እድሳት ምዝገባ ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት በይፋ መተግበር ይጀምራል። ቢሮው እንዳመለከተው ፣ ይህ የዋጋ ማስተካከያ ውሳኔ በዘፈቀደ የተወሰነ ሳይሆን በከተማዋ ሰፊ ሳይንሳዊ ጥናት ተካሂዶ የነዋሪውን እውነተኛ የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ የተዘጋጀ ነው።

"የቤት ኪራይ ከአብዛኛው ዜጎቻችን ወርሃዊ ገቢ በላይ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት በሀገራችን መካከለኛ የሚባል የህብረተሰብ መደብ ጠፍቶ ጥቂት እጅግ የበለፀጉ እና አብዛኛው በድህነት የሚማቅቅ ሁለት መደቦች ሆነዋል " - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በዘንድሮ ምርጫ ኢትዮጵያውያን በአንድ ድምጽ ጽንፈኝነት አንፈልግም፤ ባንዳነት አንፈልግም፤

በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ የምትገኝ አንዲት ወጣት በማህበራዊ ሚዲያ ባሰራጨችው አዲስ የቪዲዮ መልዕክት፣ በክልሉ ውስጥ አስደንጋጭ የሆነ የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እየተካሄደ መሆኑን አጋለጠች። ወጣቷ በቪዲዮው ላይ እንዳብራራችው፣ ህጻናትን ጨምሮ በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች ከቤተክርስቲያን፣ ከመንገድ እና ከሆቴሎች እየታፈሱ ወደ ጦርነት ማሰልጠኛዎች እየተወሰዱ ነው። ሁኔታው እጅግ አስፈሪ ደረጃ ላይ መድረሱን የምትገልጸው ይህቺ ወጣት፣ ምልመላው ማንንም የማይመርጥ መሆኑን ታስረዳለች።

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አሜሪካዊት ዜጋ የሆነችው የ29 ዓመቷ ሜላት ኪሮስ በኮሎራዶ አንደኛ ዲስትሪክት ለዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ኮንግረስ) ወንበር በተደረገው የዴሞክራቲክ ፓርቲ የመጀመሪያ ዙር የቅድመ-ምርጫ ውድድር አሸንፋለች። የረጅም ጊዜ ተመራጭ የነበሩትን ዲያና ደጌትን ያሸነፈችው 49.3% የሚጠጋ ድምጽ በማግኘት ሲሆን ደጌት ደግሞ 43.5% አግኝተዋል። በመሆኑም እ.ኤ.አ.

የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ተለይተው በታወቁ ከፍተኛ የወንጀል ስጋት ያለባቸው ቦታዎች ላይ ውጤታማ ሽፋን ለመስጠት የምድር ቡድኖችን ከሰማይ ላይ ሆነው በንቃት እያገዙ እና አደጋ ለመከላከል ዝግጁ እንደሆኑ አሳውቋል ። እነዚህ የተቀናጁ ኦፕሬሽኖች በግዛቱ ውስጥ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር፣ ወንጀልን ለመከላከል እና የሕዝብን ደህንነት ለማረጋገጥ ከሌሎች የሕግ አስከባሪ አካላት ጋር በመተባበር እየተከናወኑ ያሉ ቀጣይነት ያላቸው ጥረቶች አካል ናቸው ሲል የ ደቡብ አፍሪካ ፖሊስ አሳውቋል::
