ሊዮኔል ሜሲ ለምን ሜዳ ውስጥ አለቀሰ?

By Brook News
Jun 17, 20261 min read
315
የአርጀንቲና ኮከብ እግር ኳስ ተጫዋች Lionel Messi በ2026 የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታ ከአልጄሪያ ጋር ከተጫወቱ በኋላ ሲያለቀስ ታይቷል። ምክንያቱ ግን የጨዋታው ውጤት ወይም ከእግር ኳስ ጋር የተያያዘ ሳይሆን የግል ጉዳይ እንደሆነ ገልፆ ከሰሞኑ በበርካታ ችግሮች ውስጥ አልፍያለው ለዛ ነው ያለቀስኩት ሲል ገልጿል።
ሜሲ በጨዋታው የመጀመሪያውን ጎል ካስቆጠረ በኋላ በሜዳ ላይ በጣም ስሜታዊ ሆኖ ታይቷል። በኋላም ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር (hat-trick) አርጀንቲናን 3-0 እንድታሸንፍ አግዟል።
ይህ ክስተት ለሜሲ ታሪካዊ ጊዜ ሆኗል፤ በዓለም ዋንጫ የጎል ብዛት ሪከርድን ከጀርመኑ Miroslav Klose ጋር አስተካክሏል። እንዲሁም በ6 የዓለም ዋንጫዎች የተሳተፈ የመጀመሪያው ወንድ ተጫዋች ሆኗል።
ታድያ ሜሲ ያለቀሰው በአሸናፊነት ደስታ ብቻ ሳይሆን ከእግር ኳስ ውጭ ያሉ የግል ስሜቶች ምክንያት ነበር፤ ነገር ግን በሜዳ ላይ በልዩ አፈጻጸም ታሪክ ሰርቷል።