
ራሺያን ለመምታት ኤለን መስክ ድጋፍ ተጠየቀ❗️
🛰ራሺያን ለመምታት ኤለን መስክ ድጋፍ ተጠየቀ❗️ 👉ዘ ጋርዲያን እና ሮይተርስ እንደዘገቡት፣ የፊንላንዱ ፕሬዝዳንት ስተብ በኒውዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከኢሎን ማስክ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የስታርሊንክ (Starlink) ሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎት በሩሲያ ግዛት ውስጥም እንዲሠራ እና ዩክሬን እንድትጠቀምበት ጠይቀዋል። 👉🛰 በእጅጉ እየወደመች ያለችው ዩክሬን የአየር መከላከያ ሚሳይሎች እጥረት ስለገጠማት፣ ሩሲያ በግዛቷ ውስጥ ሆና ወደ ዩክሬን የሚሳይል ጥቃት የምታደርስባቸውን ተንቀሳቃሽ የባሊስቲክ ሚሳይል ማስወንጨፊያዎች፤ የስታርሊንክን ሳተላይት እና ድሮኖችን በመጠቀም አድራሻቸውነሰ አውቃ ቀድማ ለመምታት አቅዳለች።




