
በዓለም ላይ በዕድሜ አንጋፋው የሀገር መሪ የሆኑት የካሜሩን ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ ከህዝብ እይታ ከራቁ ሁለት ወራት ተቆጥረዋል
በዓለም ላይ በዕድሜ አንጋፋው የሀገር መሪ የሆኑት የካሜሩን ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ ከህዝብ እይታ ከራቁ ሁለት ወራት ተቆጥረዋል። እሳቸው ለቀጣይ "አጭር የግል ቆይታ ወደ አውሮፓ" ጉዞ ማድረጋቸውን የሲቪል ካቢኔያቸው ቢገልፅም ሰኔ 7 ከካሜሩን ከወጡ በኋላ እስካሁን አልተመለሱም። ታዲያ አስገርስሚው ነገር እዛው ባሉበት አውሮፓ ሆነው ከፍተኛ የወታደራዊ አባላትን ሹመት አድርገዋል :: የፕሬዝዳንታዊ ዘብ ቡድን መሪን ከኮሎኔልነት ወደ ብሪጋዴር ጄኔራልነት እና ከአገሪቱ አምስት የጋራ ወታደራዊ ክልሎች የነበሩ የአራት ክልል አዛዦችን በመተካት ከፍተኛ የወታደራዊ አባላትን ሽግሽግ አድርገዋል።


