አዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሹመቶችን አጸደቀ
A
By Ashenafi
Sep 30, 20261 min read
81
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሹመቶችን አጸደቀ
መስከረም 20፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ያቀረቧቸውን አራት ሹመቶች አጽድቋል።
በዚህም የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማዋ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል።
እንዲሁም አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ፤
አቶ ሀፍታይ ገብረእግዚአብሔር በበኩላቸው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ፤
እንዲሁም አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል።