
● LiveEducation
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ባቀረቡ ቅሬታ መሰረት በሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጊዚያዊነት እንዲመደቡ ተወሰነ።
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ባቀረቡ ቅሬታ መሰረት በሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጊዚያዊነት እንዲመደቡ ተወሰነ። ትግራይ ክልል ባለው ነባራዊ ሁኔታ በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በክልሉ አስቻይ ሁኔታ እስኪፈጠር በሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጊዚያዊነት እንዲመደቡ መወሰኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ። ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩና በአሁኑ ወቅት በክልሉ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ትምህርታቸውን መቀጠል ባለመቻላቸው ለቅሬታቸው መፍትሔ ለመጠየቅ በትምህርት ሚኒስቴር ግቢ ከተገኙ ተማሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
AAshenafi Sep 14, 20261m140