የ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ጥያቄ ና ምላሽ
By Ashenafi
Jul 7, 20261 min read
"የቤት ኪራይ ከአብዛኛው ዜጎቻችን ወርሃዊ ገቢ በላይ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት በሀገራችን መካከለኛ የሚባል የህብረተሰብ መደብ ጠፍቶ ጥቂት እጅግ የበለፀጉ እና አብዛኛው በድህነት የሚማቅቅ ሁለት መደቦች ሆነዋል " - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)
በዘንድሮ ምርጫ ኢትዮጵያውያን በአንድ ድምጽ ጽንፈኝነት አንፈልግም፤ ባንዳነት አንፈልግም፤ ዘረኝነት አንፈልግም እኛ ኢትዮጵያውያን ተባብረን የጋራ ሀገር ማጽናት፣ ማበልጸግ ነው የምንፈልገው የሚለውን በአንድ ድምጽ አስተጋብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በአርሲ ግጭት የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል'' አርሲ ዉስጥ ተከስቶ የነበረዉ ግጭት ምርጫዉን ለማደናቀፍ የተደረገ ዝግጅት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናግረዋል።
የታጠቁ ሃይሎች ውጊያ በቀጠሉበት ወቅት ምክክር ኮሚሽን ማካሄድ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የምክክር ኮሚሽኑን ሂደት በማስመልከት በሰጡት ማብራሪያ፣ የምክክር ኮሚሽን ሂደት እንዲጀመር ለረጅም ዓመት ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ጥያቄ ያላቸው ማንኛውም ዜጎች በምክክር ሂደቱ እንዲፈታ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያዊያን እጣ ፋንታ የሚወሰንበት እንዲሆን በጥንቃቄ በውጤት እና በስኬት እንዲቋጭ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

