TrendingPolitics
ጄነራል ሙሆዚ ካይኔሩጋባ ስለ ትግራይ እና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
A
By Ashenafi
Jun 16, 20261 min read
602
የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ እና የሀገሪቱ የጦር ኃይሎች አዛዥ ጄነራል ሙሆዚ ካይኔሩጋባ (Muhoozi Kainerugaba) በትግራይ ጦርነት ወቅትና ከዚያ በኋላ ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዲሁም ስለ ትግራይ ተዋጊዎች (TPLF) በትዊተር (X) ገጹ ላይ በርካታ አነጋጋሪ አስተያየቶችን ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል። ዛሬም በኤክስ ገጻቸው ላይ ያሰፈሩት መልዕክት መነጋገሪያ ሆኗል እንዲህም ብለዋል "በትግራይ የሚገኙ ታላላቅ ወንድሞቼ ሌላ ጦርነት እንዳይጀምሩ እለምናቸዋለሁ። በጣም እወዳቸዋለሁ ነገር ግን ጦርነት ሰልችቶናል። በዚህ ጊዜ ወንድሜን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን እደግፋለሁ።"
