ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መግባት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ?
A
By Ashenafi
Sep 9, 20261 min read
191
🇺🇸ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መግባት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን የፍልሰት ጉዳዮች ለማስተናገድ፤ የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት በኢትዮጵያ የሚከፍተው ቢሮ በነገው ዕለት ስራ ይጀምራል።
👉በቢሮው ለመስተናገድ የሚሹ ኢትዮጵያውያን አስቀድመው ቀጠሮ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው አገልግሎቱ ገልጿል።
👉መቀመጫውን በአዲስ አበባ የሚያደርገው አዲሱ ቢሮ ለቪዛ ማመልከቻዎች ውሳኔ የሚሰጥ እንዳልሆነ የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት አስታውቋል።
👉ሆኖም ቢሮው ኢትዮጵያውያን ለፍልሰት ማመልከቻዎቻቸው የሚያቀርቧቸውን ሰነዶች ትክክለኛነት የማረጋገጥ ስራን የሚያከናውን መሆኑን አገልግሎቱ አስገንዝቧል።
👉የተጠረጠሩ የሰነድ “ማጭበርበሮችን” የሚመረምሩት እና የቤተሰቦችን ዝምድና ለማረጋገጥ የዘረ-መል (DNA) ናሙናዎችን የሚሰበስቡት በአዲስ አበባ የሚከፈተው የአገልግሎቱ ቢሮ ሰራተኞች ይሆናሉ።
👉እነዚህ ስራዎች ከዚህ ቀደም ሲከናወኑ የነበረው፤ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት እንደነበር ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ጠቁሟል።
🇺🇸የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት “ወሳኝ የስራ ኃላፊነቶች” ያላቸውን እነዚህን ተግባራት፤ አዲሱ ቢሮ “በቀጥታ ለማከናወን የሚያስችለውን ልዩ ውክልና ይሰጠዋል” ተብሏል።