● LiveCrime
የመኪናው ስፖንዳ ወደ ላይ በላሜራ ከፍ በማድረግ የመደበቂያ ቦታ በማዘጋጀት ነዳጅ ለማሸሽ የሞከሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ ::
A
By Ashenafi
Jun 28, 20261 min read
334
የመኪናው ስፖንዳ ወደ ላይ በላሜራ ከፍ በማድረግ የመደበቂያ ቦታ በማዘጋጀት በ ህገወጥ መንገድ በ6 ታንከሮች (ተሳቢዎች) ላይ ተጭኖ ሊወጣ የነበረ ነዳጅ፣ ነዳጁን የጫኑት ተሽከርካሪዎች እና አሽከርካሪዎቻቸው በአፍሔራ ወረዳ ፖሊስ በተደረገ ጠንካራ ክትትልና ፍተሻ በቁጥጥር ሥር ውለው ጥብቅ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ተዘግቧል ።
የአፍሔራ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ውጪ በተለያዩ ዘዴዎች ሊወጣ የነበረ ነዳጅ እና ነዳጁን የጫኑ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አስታውቋል።
የአፍሔራ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ሳጂን መሐመድ ዓሊ እንደገለጹት፤ በሕገ-ወጥ መንገድ በ6 ታንከሮች (ተሳቢዎች) ላይ ተጭኖ ሊወጣ የነበረ ነዳጅ፣ ነዳጁን የጫኑት ተሽከርካሪዎች እና አሽከርካሪዎቻቸው በአፍሔራ ወረዳ ፖሊስ በተደረገ ጠንካራ ክትትልና ፍተሻ በቁጥጥር ሥር ውለው ጥብቅ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አረጋግጠዋል።