
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል እና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ በማላዊ አድኖ ያዘ ::
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል እና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር፣ በብዙ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ላይ ከፍተኛ ኢሰብአዊ ድርጊት ሲፈጽም የነበረውን አድነው ባሻው ውዳሞ የተባለ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ በማላዊ አድኖ በቁጥጥር ሥር በማዋል ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ እንዳመጣው አሳወቀ። ተጠርጣሪው ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል (በተለይም ከሀድያ እና ከንባታ ዞኖች) ወጣቶችን "ሕይወታችሁን ታሻሽላላችሁ" በሚል አታልሎ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያዘዋውር የነበረ ሲሆን፣ ከእያንዳንዱ ተጓዥ ከ600 ሺህ እስከ 800 ሺህ ብር ይጠይቅ ነበር። ተጓዦችን በዕቃ መጫኛ ኮንቴነሮች፣ በተሳቢ እና በሸራ በተሸፈኑ መኪኖች አጭቆ ወደ ታንዛኒያ ካሻገረ በኋላ ጫካ ውስጥ ጥሏቸው ይፈረጥጥ ነበር።

