
TrendingFootball
በእግር ኳስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ የእረፍት ሰዓት እስከ 25 ደቂቃ ሊረዝም እንደሚችል ታውቋል።
በእግር ኳስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ (ፋይናል) ጨዋታ የእረፍት ሰዓት (Half-time)፣ የአሜሪካው 'ሱፐር ቦውል' አይነት ታላቅ የሙዚቃ ትዕይንት ለማስተናገድ ሲባል እስከ 25 ደቂቃ ሊረዝም እንደሚችል ታውቋል። ይህ ታሪካዊ ክስተት እሑድ በኒው ዮርክ ኒው ጀርሲ ስታዲየም በሚደረገው የ2026 ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ ይካሄዳል። ይህንን የሙዚቃ ትዕይንት የኮልድፕሌይ (Coldplay) ባንድ መሪ ክሪስ ማርቲን ያዘጋጀው (curate ያደረገው) ሲሆን፣ በዓለም ዙሪያ እጅግ ዝነኛ የሆኑ አርቲስቶች በአንድ መድረክ ላይ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
AAshenafi 1d ago1m55
