ReportAfrica
በዓለም ላይ በዕድሜ አንጋፋው የሀገር መሪ የሆኑት የካሜሩን ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ ከህዝብ እይታ ከራቁ ሁለት ወራት ተቆጥረዋል
A
By Ashenafi
Aug 5, 20261 min read
209
በዓለም ላይ በዕድሜ አንጋፋው የሀገር መሪ የሆኑት የካሜሩን ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ ከህዝብ እይታ ከራቁ ሁለት ወራት ተቆጥረዋል።
እሳቸው ለቀጣይ "አጭር የግል ቆይታ ወደ አውሮፓ" ጉዞ ማድረጋቸውን የሲቪል ካቢኔያቸው ቢገልፅም ሰኔ 7 ከካሜሩን ከወጡ በኋላ እስካሁን አልተመለሱም። ታዲያ አስገርስሚው ነገር እዛው ባሉበት አውሮፓ ሆነው ከፍተኛ የወታደራዊ አባላትን ሹመት አድርገዋል :: የፕሬዝዳንታዊ ዘብ ቡድን መሪን ከኮሎኔልነት ወደ ብሪጋዴር ጄኔራልነት እና ከአገሪቱ አምስት የጋራ ወታደራዊ ክልሎች የነበሩ የአራት ክልል አዛዦችን በመተካት ከፍተኛ የወታደራዊ አባላትን ሽግሽግ አድርገዋል።
ሹመቶቹ የአስቸኳይ ጊዜ ጣልቃ-ገብነት ሲሆን አዲስ አዛዥ የሜጀር ጄኔራል ወደ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ መሪያነት እድገት የበርካታ ኮሎኔሎች ወደ ብሪጋዴር ጄኔራልነት ማዕረግ ማደግ እንዲሁም በሞተረኛ እግረኛ ጓዶች ላይ የተደረጉ ለውጦችን ያካተቱ ናቸው። ምንጭ TRT Afrika

