
የ ቅዱስ ፓትርያርኩ የጾመ ማርያም (የጾመ ፍልሰታ) መልእክት
ቅዱስ ፓትርያርኩ የጾመ ማርያም (የጾመ ፍልሰታ) ወቅት ባስተላለፉት መልእክት የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አጉልተው አሳስበዋል ምዕመናን የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ የታመሙትንና የታሰሩትን በመጠየቅ፣ እንዲሁም ንስሐ በመግባትና ቅዱስ ቁርባን በመቀበል እንዲያሳልፉ አባታዊ ጥሪ አቅርበዋል። አምላክን መውደድ በስሜት ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን ትእዛዛቱን በመጠበቅና በመተግበር የሚረጋገጥ ተግባራዊ ሕይወት እንደሆነ ገልጸዋል። ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ» ሲባል የተወሰነ የኅብረተሰብ ክፍልን ብቻ ሳይሆን በሕይወት ያሉትንም ሆነ ያለፉትን—መላውን የሰው ልጅ የሚያጠቃልል እንደሆነ አብራርተዋል።
AAshenafi Aug 6, 20261m135