● LivePublic Health
200 የሚደርሱ ተማሪዎች ላይ የደርሰ ድንገተኛ ህመም እና ወቅታዊ የጤና ሁኔታ
A
By Ashenafi
Jun 26, 20261 min read
320
በደቡብ ኣሪ ወረዳ ሜፀር መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በተከሰተ ድንገተኛ ህመም ምክንያት ራሳቸውን የሳቱና ያስመልሳቸው የነበሩ በግምት እስከ 200 የሚደርሱ ተማሪዎች ወደ ጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ገብተዋል።
በተደረገላቸው አስቸኳይ ህክምና አብዛኞቹ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከፍተኛ ክትትል የሚያስፈልጋት አንዲት ተማሪ ብቻ ወደ ጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል በሪፈራል ተልካለች።
የህመሙ መነሻ ምክንያት (ከተጠቀሰው ጁስ ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ መሆኑን) ለማረጋገጥ የላብራቶሪና የሙያዊ ምርመራ በጥልቀት እየተካሄደ ነው። ሁኔታው ሙሉ በሙሉ በሆስፒታሉ ቁጥጥር ስር በመሆኑ ወላጆችና ማህበረሰቡ ሳይደናገጡ እንዲረጋጉ የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስተዳደር አሳውቀዋል።
Filed under