
የ100 ግራም ወርቅ ፉክክር፡ ጉርሻ ፔጅ ለዓመቱ ታላቅ ሽልማት እጩ ሆኖ ቀረበ!
የ100 ግራም ወርቅ ፉክክር፡ ጉርሻ ፔጅ ለዓመቱ ታላቅ ሽልማት እጩ ሆኖ ቀረበ! በጉጉት የሚጠበቀው የቅን ልቦች የዓመት በጎ ተሸላሚ"ውድድር የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል። በነሐሴ ወር በሚካሄደው በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ፣ አሸናፊው የ100 ግራም ንጹሕ ወርቅ ተሸላሚ እንደሚሆን ታውቋል።
Section
What's happening in your city.
3 stories
Latest in Local
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአርሲ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያን እና በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ :: "በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ስለደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የሰማነው በተሰበረ ልብ ነው። ይህ መከራ እያበቃ ሳይሆን እየሰፋ በመምጣቱ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባችሁ የጸጥታ አካላትና በየመዋቅሩ ያላችሁ ሓላፊዎች ከምንም በላይ ታሪክ የሚጠይቃችሁ በሥልጣን ዘመናችሁ ለዜጎች ደኅንነት በምትከፍሉት ዋጋ ነውና ይህንን የጥቃት ሰንሰለት በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የአርሲና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት 13 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን፣ ከ280 በላይ ምእመናን መፈናቀላቸውንና የ101 ዓመት ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን አሳወቁ። ብፁዕነታቸው በደረሰው ጥቃት ሐዘናቸውን ገልጸዋል:: ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ:ም ጀምሮ በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ ወረዳ; በሺርካ ወረዳና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 13 ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ የ101 ዓመት እድሜ ያለው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል። ዘገባው የአርሲ ሀገረ ስብከት ሚድያ ነው

Jun 8, 2026