● LivePolitics
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያቀረበው አቤቱታ
A
By Ashenafi
Aug 11, 20261 min read
164
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያቀረበው አቤቱታ እና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ!
በምክክሩ ወቅት አዳዲስ ተሳታፊዎች ግልጽነት በጎደለው መንገድ እየተጨመሩ መሆኑን፣ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ከተመደቡበት ቡድን ውጭ በመግባት ተፅዕኖ እያሳደሩ እንደሚገኙ እና ሂደቱ ቀድሞ ወደተወሰነ የፖለቲካ አቅጣጫ እየተመራ ነው ሲል አብን ይከሳል።
የባለሙያዎች ፓነል ገለልተኝነት የጎደለው መሆኑን እና የአንድን ወገን የፖለቲካ ትርክት ለማስረጽ እንደሚሞክርም የ አብን ደብዳቤ ይገልጻል።
በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የሚደረገው ውይይት በቁጥር ብልጫ ሌላውን ለመጫን የሚደረግ አካሄድ ይታይበታል ሲል ይገልጻል። በመሆኑም ጉዳዩ ሀገሪቱን ወደ ባሰ ውጥረት ውስጥ ስለሚከተው፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚደረገው ንግግር በአስቸኳይ እንዲቆም እና አጀንዳው እንዲያርፍ ይጠይቃል
አብን ኮሚሽኑ እነዚህን መሠረታዊ ስጋቶች ችላ ብሎ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ የሚሸጋገር ከሆነ፣ ፓርቲው ለሂደቱ ሕጋዊነት ላለመስጠት ሲል ከምክክሩ ሙሉ በሙሉ ከመውጣት ጀምሮ አስፈላጊውን የፖለቲካ አቋም የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን አስጠንቅቋል።

