● LivePolicy
በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ ተወሰነ
A
By Ashenafi
Jul 8, 20261 min read
273
ከዚህ ቀደም በወጣው የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅ መሠረት፣ ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበረው ፍትሐዊ የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ መጽደቁን የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
ይህንን ተከትሎ በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል እድሳት ምዝገባ ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት በይፋ መተግበር ይጀምራል።
ቢሮው እንዳመለከተው ፣ ይህ የዋጋ ማስተካከያ ውሳኔ በዘፈቀደ የተወሰነ ሳይሆን በከተማዋ ሰፊ ሳይንሳዊ ጥናት ተካሂዶ የነዋሪውን እውነተኛ የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ የተዘጋጀ ነው። ውሳኔው በከተማዋ ያለውን የኑሮ ውድነት ጫና በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ ረገድ የጎላ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና መልካም አስተዳደር ፋይዳዎች እንዳሉት ተገልፃል::