በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የወጣ መመሪያ ና ማሻሻያ
By Ashenafi
6d ago1 min read
ከ2010 ዓ.ም ጀምረው እስከ 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ሳይፈተኑ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ የሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም የሶስተኛ ዲግሪ የያዙ ባሉበት የትምህርት (ለBA, MA, and PhD) ደረጃ ላይ ሚኒስትሩ በሚያወጣው በያዙት የትምህርት ደረጃ ፈተና ተፈትነው ሲያልፉ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው ይሆናል፡፡
በቀድሞው ዲፕሎማ ወይም ከ12+2 ወይም ከ10+3 ወይም ከቴክኒክና ሙያ ደረጃ አራት ስልጠና ተመርቀው ያጠናቀቁ ትክክለኛነቱ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወይም በፌደራል ወይም በክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም የተረጋገጠ ኦሪጅናል የስልጠና ማስረጃ ወይም ዲፕሎማ እና ትራንስክሪፕት ኖራቸው ነገር ግን የደረጃ አራት የብቃት ማዕቀፍ ሳይኖራቸው በመጀመሪያ ዲግሪ ተምረው የተመረቁ የትምህርት ማስረጃ የሚረጋገጥላቸው፦
ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ይህ መመሪያ እስከተሻሻለበት ጊዜ የተመረቁ እና የመውጫ ፈተና ተፈትነው ያለፉ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው ይሆናል።
ይህ መመሪያ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ማንኛውም የመንግስት እና የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ከመስከረም 2010 እስከ 2015 ዓ.ም. የተመረቁ ተመራቂዎች ብቻ የሚተገበር ሲሆን፦
ለዲግሪ መግቢያ መስፈርት የተቀመጠውን የደረጃ አራት የብቃት ማረጋገጫ ፈተና (ሲ.ኦ.ሲ.) ሳይወስዱ ዲግሪ ተምረው የተመረቁትን፣ ወይም
ለዲግሪ ትምህርት ከተመዘገቡ በኋላ የደረጃ አራት የብቃት ማረጋገጫ (ሲ.ኦ.ሲ.) ፈተና የወሰዱትን ተመራቂዎች ያጠቃልላል፡፡