● LiveFootball
ቶማስ ፓርቴ ወደ ካናዳ እንዳይገባ ታገደ!
A
By Ashenafi
Jun 13, 20261 min read
477
ቶማስ ፓርቴ ወደ ካናዳ እንዳይገባ ታገደ!
የፊፋ (FIFA) እና የካናዳ መንግሥት እንዳረጋገጡት የጋናው አማካኝ ተጫዋች ቶማስ ፓርቴ ወደ ካናዳ ለመግባት ያደረገው የቪዛ ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል። በዚህም ምክንያት ወደ ሀገሪቱ እንዳይገባ የታገደ ሲሆን በቶሮንቶ ከፓናማ ጋር የሚደረገውን የ2026 ዓለም ዋንጫ መክፈቻ ጨዋታ ያመልጠዋል።
ፓርቴ በአሜሪካ በሚገኘው የጋና የልምምድ ማዕከል የሚቆይ ሲሆን በአሜሪካ ለሚደረጉ ጨዋታዎችም ብቁ ነው:: ወደ አሜሪካ ለመግባት ቪዛ የተሰጠው በመሆኑ ጋና በአሜሪካ መሬት ላይ ለምታደርጋቸው ቀጣይ የምድብ ጨዋታዎች መሰለፍ ይችላል።የካናዳ መንግሥት የፓርቴን የቪዛ ጥያቄ ውድቅ ያደረገው በዩናይትድ ኪንግደም ካለበት ህጋዊ ክስ ጋር በተያያዘ ነው።

